የፓርቲው አባል ለመሆን መመዘኛዎች

የብልጽግና ፓርቲ አባል ለመሆን ከዚህ በታች የተመለከቱትን መመዘኛዎች የሚያሟላ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የፓርቲው አባል መሆን ይችላል።

  1. የፓርቲውን ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ተቀብሎ በጽናት ተግባራዊ ለማድረግ ፍቃደኛ የሆነ፤
  2. መልካም ሥነ-ምግባር ያለውና በኅብረተሰቡ ውስጥ ተቀባይነት ያለው፤
  3. በኅብረ ብሔራዊነት እና በሀገራዊ አንድነት ላይ ጽኑ አቋም ያለውና ዋልታ-ረገጥ አመለካከትና ተግባሮችን በጽናት የሚታገል፤
  4. ዜጎችንና ሕዝቦችን በእኩልነት የሚያገለግል፣ የሕዝብ ጥቅምን የሚያስቀድም፣ከሙስናና ብልሹ አሠራሮች ራሱን ያራቀና ሌሎችንም የሚታገል፤
  5. የፓርቲውን ዕሴቶችና ዓላማዎችን ተቀብሎ የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት ቁርጠኛ የሆነ፤
  6. ወርኃዊ የአባልነት ክፍያ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ፤
  7. እድሜ 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ፤
  8. የሌላ ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ፤
  9. የፖለቲካ ፓርቲ አባል የመሆን መብቱ በሕግ ያልተገደበ ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔ ያልተገፈፈ፤
  10. በዚህ ደንብ በተወሰነው መሠረት የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ የፓርቲው አባል መሆን ይችላል።